በ2022 ዓ.ም ዘመናዊ የመስሪያ ቦታ በማልማት አቅርቦቱን በማፋጠንና አስተዳደራዊ አሰራሩን በማዘመን በዘርፉ የተሰማሩ ኢንተርፕራዞች እና ኢንዱስትሪዎች ኢኮኖሚያዊ ተጠቃሚነት ተረጋግጦ ማየት ፡፡
የዘርፉን እድገት ያማከለ ተጨባጭ ጥናት ላይ የተመሰረተ እና መሰረተ ልማት የተሟላላት ደረጃውን የጠበቀ የመስሪያ ቦታ ገንብቶ በማስተላለፍ እና ፈጣን አገልግሎትን መሰረት ያደረገ ዘመናዊ አስተዳደርን በመዘርጋት የኢንተርፕራዞች እና አምራች ኢንዱስትሪዎችን ተጠቃሚነት ማረጋገጥ ነው፡፡
ይሁንና ለስራ ፈላጊ ዜጎች የሚያስፈልጓቸውን ድጋፎች በማመቻቸት የስራ እድል ፈጠራ ስራው ውጤታማ ቢሆንም በዘርፉ በከፍተኛ ቁጥር እያደገ የመጣውን የዜጎች የስራ ዕድል ይፈጠርልኝ ጥያቄ ለመመለስ የሚያስችል የአሰራር ስርዓት መዘርጋት፣ ማሻሻል እና በውጤታማነት መምራት አስፈላጊ መሆኑን በመረዳት በ2017 በጀት አመት መንግስታዊ ድጋፎችን እና አገልግሎቶችን በተቀናጀ መልኩ በቁርጠኝነት አጠናክሮ በመስጠት ላይ እንገኛለን፡፡...
የልደታ ክፍለ ከተማ ወረዳ 02 አስተዳደር ካቢኔ አባላት ውሳኔ በሚያስፈልጋቸው ጉዳዮች ዙሪያ ተወያይቶ እታች ድረስ በመውረድ ውሳኔ ሰጥቷል፡፡ መድረኩን የመሩት የልደታ ክፍለ ከተማ ወረዳ 02 አስተዳደር ዋና ስራ አስፈጻሚ አቶ ሃምዛ ከድር እንደገለጹት በወረዳው ነዋሪዎች የቀረቡ የመልካም አስተዳደር ጥያቄዎች ተገቢነት ዙሪያ ውይይት ማድረጉና እንደ አግባቡ ጥያቄያቸው ምላሽ እንዲያገኝ የወረዳው አስተዳደር እንደሚሰራ ገልጸዋል። ...
ከወረዳው ብሎክ ክውንስል ሰብሳቢዎች ጋር በስራ እድል ፈጠራ እና በተጠቃሚነት ዙሪያ የግንዛቤ ፈጠራ ማስጨበጫ ስልጠና ሰጠ። መድረኩን የመሩት የስራና ክህሎት ጽህፈት ቤት ሃላፊ ወ/ሮ ላምሮት ቀውዬ እንደገለጹት ጽህፈት ቤቱ የወረዳውን ሴቶች፣ ወጣቶች እና ስራ አጦችን በስራ እድል ተጠቃሚ ለማድረግ በዋናነት እቅድ ይዞ እየሰራ መሆኑን የገለፁ ሲሆን የካውንስሉ ሰብሳቢዎች በየብሎካቸው ...
የመክፈቻ ንግግር ያደረጉት የፅ/ቤቱ ሃላፊና ም/ስራ አስፈፃሚ ወ/ሮ ላምሮት ቀውዬ እንደገለፁት በትንሽ ገንዘብ ራስን ማሳደግ እንደሚቻል ጠቅሰው በትንሽ ገንዘብ ሚሊየነር የሆኑ አሉ ብለዋል። አያይዘውም ከእናንተ ተስፋ ያለመቁረጥና የዓላማ ፅናት እንደሚያስፈልገ ገልፀው በሰለጠማችሁበት ሙያ መስራት አለባችሁ ብለዋል። የፅ/ቤቱ የአንድ ማዕከል የስራዎች አስተባባሪ ....
የከተማችንን ብሎም የክ/ከተማችን ነዋሪ ፈጣን፣ ተደራሽ እና ጥራት ያለው አገልግሎት የማግኘት መብት ያለው በመሆኑ ይህንን የህዝባችንን ፋላጎት ዕውን ከማድረግ አኳያ የአገልገሎት አሰጣጡን ቀልጣፋና ዘመናዊ ማድረግ እንዲሁም ቀጣይነት ባለው መልኩ ራሱን እያሻሻለ እና እያሰደገ የሚሄድ በስነምግባሩ የተመሰገነ ...
በሀገር ደረጃ የተጀመረዉን ሪፎርም በማስረጽ የአገልግሎት አሰጠጡን ተደራሽ፣ ግልጽና ወጪ ቆጣቢ በማድረግ የጽ/ቤቱን ራዕይ እና ተልዕኮ ለማሳካት ዘመን የወለዳቸውን የቴክኖሎጂ ዉጤቶች አቀናጅቶ ውጤታማ ስራ ለማከናወን እየተደረገ ያለዉ እንቅስቃሴ ከመቼውም ጊዜ በላይ የተሻለ ነዉ፡፡
የስራ አካባቢን ሳቢ ፣ ፅዱና ምቹ ከማድረግ ጋር ተያይዞም በጽ/ቤቱ ለአገልግሎት አሰጣጥ ከፍተኛ ችግር ፈጥሮ የነበረውን የተከማቸ ፋይል በማንሳት ፤ የካይዘንን ፍልስፍና ተግባራዊ በማድረግ የፈጻሚውን አቀማመጥ በማስተካከል ችግር የነበረባቸውን የፈጻሚ ወንበሮች በመለወጥና በማደስ ቢሮውን የማሳመር ስራ ተሰርቷል፡፡
Visit our Web App
በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የአገልግሎት ሰጪ ተቋማትን መልሶ ለማደራጀት በወጣ አዋጅ መሰረት የስራና ክህሎት ጽ/ቤት እንደገና የተቋቋመ ሲሆን ከተሰጠው ተግባርና ኃላፊነት መነሻ
የመልካም አስተዳደር ችግሮችን በዘላቂነት ለመፍታትና የለውጥ ሥራዎችን ቀጣይነት ለማረጋገጥ የተቋሙን አገልግሎት አሰጣጥ ክትትልና ድጋፍ በማድረግ በብቃቱና እና በሥነ-ምግባሩ የተመሰገነ የሰው ኃይል እንዲመራ በማድረግ ለተገልጋዮቹ የሚሰጣቸውን አገልግሎቶች በአዲስ መልክ በመለየት አደራጅቷል፡፡
በተጨማሪም
በወረዳዉ ስራና ክህሎት ጽ/ቤት የሚሰጠው አገልግሎት የተገልጋይ ፍላጎትን ማዕከል አድርጎ ይበልጥ ተደራሽ እንዲሆን ለማስቻል የሚሰጡ አገልግሎት አይነቶች፣ አገልግሎቱ የሚሰጥበት ስታንዳርድ፣ የሚሰጥበትን ቦታ እና ከተገልጋይ የሚጠበቁ ቅድመ ሁኔታዎችን በግልጽ በዝርዝር በማስቀመጥ የጽ/ቤቱ አመራር ሠራተኞች አገልግሎቶቹን በተቀመጠላቸው ስታንዳርድ መሰረት ፍህታዊና ቀልጣፋ አገልግሎት እንዲሰጡና ተገልጋዮች ምን ዓይነት አገልግሎት በምን ዓይነት ደረጃ ማግኘት እንደሚገባቸው...
If you have any question please do not hesitate to call or contact us. Our Address is
Tor hailoch 18 roundabout, Lideta Woreda 2 Administration Building 1st Floor, Addis Ababa, Ethiopia.
Phone: +251118134145
Email: 2022
© 2024 Lideta Labor and Skills Office. Designed by Markos MG 0912689710.